ኢያሱ 22:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 “እኛም፣ ‘ወደ ፊት እኛንም ሆነ ዘሮቻችንን እንዲህ የሚሉ ከሆነ፣ “እነሆ፤ አባቶቻችን የሠሩትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ ተመልከቱ፤ ይህ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር እንዲሆን እንጂ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለሌላ መሥዋዕት ማቅረቢያ አይደለም” ብለን እንመልሳለን’ አልን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ስለዚህም እንዲህ አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ እኛ እንዲህ እንላለን፦ ‘እነሆ፥ አባቶቻችን የሠሩትን የጌታን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለማቅረብ አይደለም።’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 እንግዲህ ምናልባት ይህ ነገር ቢሆን የእኛ ዕቅድ፥ ዘሮቻችን፦ ‘ተመልከቱ! የቀድሞ አባቶቻችን የሠሩት መሠዊያ ለእግዚአብሔር ከተሠራው መሠዊያ ጋር አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም በእኛና በእናንተ ሕዝቦች መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር እንጂ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት እንዲቀርብበት ታስቦ አልነበረም’ ማለት እንዲችሉ ነው፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ኋላ ይህ በተደረገ ጊዜ ነገ ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ፥ እኛ፦ እነሆ፥ አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ቍርባን አይደለም እንላለን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን ይህን ሲሉ እኛ፦ እነሆ፥ አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዩ፥ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት አይደለም እንላለን። Ver Capítulo |