Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 7:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ይኸው እርሱ በአደባባይ ይናገራል፤ አንድም ቃል አይናገሩትም፤ ክርስቶስ ነው ብለው ባለሥልጣኖቹም ተቀብለውት ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እነሆ፥ በግልጥ ይናገራል፤ ነገር ግን ምንም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው ክርስቶስ እንደሆነ በእውነት አወቁን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እነሆ፥ እርሱ በግልጥ ይናገራል፤ እነርሱም ምንም አላሉትም፤ ይህ ሰው መሲሕ መሆኑን ባለሥልጣኖች በእውነት ዐውቀው ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነሆ፥ እርሱ በገ​ሀድ ይና​ገ​ራል፤ እነ​ርሱ ግን ምንም የሚ​ሉት የለም፤ ይህ በእ​ው​ነት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ምና​ል​ባት አለ​ቆች ዐው​ቀው ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እነሆም፥ በግልጥ ይናገራል አንዳችም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ በእውነት አወቁን?

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 7:26
21 Referencias Cruzadas  

ለመሆኑ ከባለሥልጣኖችና ከፈሪሳውያን በርሱ ያመነ አለ?


በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ካሉት ወንድሞች ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሀት፣ በድፍረት ለመናገር ብርታት አግኝተዋል።


ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋራ እንደ ነበሩም ተገነዘቡ።


ይህም ቢሆን፣ ከአለቆች መካከል እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በርሱ አመኑ፤ ይሁን እንጂ ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያስወጧቸው ስለ ፈሩ ማመናቸውን አይገልጡም ነበር።


ኢየሱስን፣ ክርስቶስ ነው ብሎ የመሰከረ ሁሉ ከምኵራብ እንዲባረር አይሁድ አስቀድመው ወስነው ስለ ነበር፣ ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁድን ፈርተው ነው።


ፈሪሳውያንና ሕግ ዐዋቂዎች ግን በዮሐንስ እጅ ባለመጠመቃቸው፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ዐላማ አቃለሉ።


ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋራ ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉን እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤


ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”


ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።


ጲላጦስም የካህናት አለቆችን፣ ገዦችንና ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቦ፣


ከፈሪሳውያን ወገን፣ ከአይሁድ አለቆች አንዱ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ ሰው ነበረ፤


“ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” አለች፤


በዚህ ጊዜ በኢየሩሳሌም የነበሩ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ አሉ፤ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለምን?


ሆኖም ከሕዝቡ ብዙዎች በርሱ አምነው፣ “ታዲያ፣ ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ከሚሠራቸው ታምራዊ ምልክቶች የበለጠ ያደርጋል?” አሉ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios