Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 14:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም እመኑ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኑ፤ በእ​ኔም እመኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 “ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 14:1
37 Referencias Cruzadas  

ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ አዳኜና አምላኬን፣ ገና አመሰግነዋለሁና።


እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።


በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።


በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች።


ኢየሱስም እርሷ ስታለቅስ፣ ተከትለዋትም የመጡት አይሁድም ሲያለቅሱ ባየ ጊዜ መንፈሱ በሐዘን ታውኮ፣


“አሁንስ ነፍሴ ተጨነቀች፤ ምን ልበል? አባት ሆይ፤ ከዚህች ሰዓት ብታድነኝስ? ይሁን፤ የመጣሁት ለዚህች ሰዓት ነውና።


ከዚያም ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “ማንም በእኔ ቢያምን በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ማመኑ ነው፤


“ሲፈጸም እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፣ ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ነገርኋችሁ።


እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።


ይህን ሁሉ የሚያደርጉባችሁ፣ አብን ወይም እኔን ስላላወቁ ነው።


ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፤


ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።


የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”


ደግሞም ከልክ በላይ ዐዝኖ ተስፋ እንዳይቈርጥ፣ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባችኋል።


ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነት፣ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንሥቶ፣


በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደ ተላከ መልእክት የጌታ ቀን ደርሷል ብላችሁ ፈጥናችሁ ከአእምሯችሁ አትናወጡ፤ አትደንግጡም።


በርሱም አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ፤ ስለዚህ እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos