Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 4:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “በዚያ ቀን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ንጉሡና ሹማምቱ ወኔ ይከዳቸዋል፤ ካህናቱ ድንጋጤ ይውጣቸዋል፤ ነቢያቱም ብርክ ይይዛቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “በዚያም ቀን፥ ይላል ጌታ፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይሣቀቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ቀን ንጉሡና ባለሟሎቹ ፍርሀት ያድርባቸዋል፤ ካህናት ይንቀጠቀጣሉ፤ ነቢያትም ይደነግጣሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በዚ​ያም ቀን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የን​ጉ​ሡና የመ​ኳ​ን​ንቱ ልብ ይጠ​ፋል፤ ካህ​ና​ቱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ ነቢ​ያ​ቱም ያደ​ን​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፥ ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 4:9
20 Referencias Cruzadas  

ምንም እንኳ ባቢሎናውያን ከተማዪቱን እንደ ከበቧት ቢሆንም የከተማዪቱ ቅጥር ተጣሰ፤ ሰራዊቱም ሁሉ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ባሉት በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በዓረባ በር ዐልፎ በሌሊት ሸሸ፤ ሽሽቱም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር።


ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።


በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።


የግብጻውያን ልብ ይሰለባል፤ ዕቅዳቸውንም መና አስቀራለሁ፤ እነርሱም ጣዖታትንና የሙታንን መናፍስት፣ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ምክር ይጠይቃሉ።


በመጣ ቍጥር ይዟችሁ ይሄዳል፤ ማለዳ ማለዳ፣ በቀንና በሌሊትም ይጠራርጋል።” ይህን ቃል ብታስተውሉ፣ ሽብር በሽብር በሆነ ነበር።


“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣ የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣ ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ።


እናንተ እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤ እናንተ የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ የምትታረዱበት ቀን ደርሷልና፤ እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰከሳላችሁ።


ለመሆኑ፣ ‘የባቢሎን ንጉሥ እናንተንም ይህችንም ምድር አይወጋም’ ብለው ትንቢት ይናገሩ የነበሩት ነቢያታችሁ ወዴት ናቸው?


ከተሞቹ ይወረራሉ፤ ምሽጎቹም ይያዛሉ፤ በዚያ ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወድዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?”


የከተማዪቱም ቅጥር ተነደለ፤ ሰራዊቱም ሁሉ ኰብልሎ ሄደ። ባቢሎናውያን በከተማዪቱ ዙሪያ ቢኖሩም፣ በንጉሡ የአትክልት ስፍራ አጠገብ በሁለት ቅጥሮች መካከል ባለው በር በሌሊት ከተማዪቱን ጥለው ሸሹ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።


“ ‘እናንተ ፌዘኞች፤ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም ቢነግራችሁ እንኳን፣ የማታምኑትን ነገር፣ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos