Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 39:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፦ የሳምጋሩ ኤርጌል ሳራስር፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቦሠርሰኪም፣ ከፍተኛው ሹም ኤርጌል ሳራሳር እንዲሁም ሌሎቹ የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋር ናቦ፥ የራፌሱ ሠርሰኪም፥ የራብማጉ ኤርጌል ሳራስር፥ ከተረፉት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የኢየሩሳሌም ከተማ በተያዘች ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ባለ ሥልጣኖች መጥተው በመካከለኛው ቅጽር በር ስፍራ ስፍራቸውን ያዙ፤ ከእነርሱም መካከል፥ ኔርጋልሻሬጼር፥ ሣምጋር ነቦ፥ ሣርሰኪምና ሌላው ኔርጋልሻሬጼርና እንዲሁ ሌሎችም ይገኙባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ፥ ማር​ጋ​ና​ሳር፥ ሳማ​ጎት፥ ናቡ​ሳ​ኮር፥ ናቡ​ሰ​ሪስ፥ ናግ​ራ​ጎ​ስ​ና​ሴር፥ ረብ​ማግ፥ ኔር​ጋል ሴሪ​አ​ጼር፥ ከቀ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ጋር ገብ​ተው በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው በር ውስጥ ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 39:3
6 Referencias Cruzadas  

ከባቢሎን የመጡት ሱኮት በኖትን፣ ከኩታ የመጡት ኔርጋልን፣ ከሐማት የመጡት አሲማትን ሠሩ፤


እነሆ፤ የሰሜን መንግሥታትን ሕዝቦች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ንጉሦቻቸው ይመጣሉ፤ ዙፋናቸውን በኢየሩሳሌም መግቢያ በሮች፣ በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ይዘረጋሉ።


‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን የባቢሎንን ንጉሥና ባቢሎናውያንን ለመውጋት በእጃችሁ የያዛችሁትን የጦር መሣሪያ በእናንተው ላይ አዞራለሁ፤ ወደዚህችም ከተማ ሰብስቤ አስገባቸዋለሁ።


ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ።


የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቡሸዝባን፣ ከፍተኛ ሹሙ ኤርጌል ሳራስር እንዲሁም ሌሎች የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፣


ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ ዐቧራ ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደ ፈረሱ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፣ ከፈረሶቹና ከጋሪዎቹ፣ ከሠረገሎቹም ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos