Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 27:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የርሱ አገር በተራው ለሌሎች እስከሚገዛበት ጊዜ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ለርሱ፣ ለልጁና ለልጅ ልጁ ይገዛሉ፤ በዚያ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችና ታላላቅ ነገሥታት እርሱን ይገዙታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በራሱ ምድር ላይ መውደቅያው እስከሚመጣ ጊዜ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁም ለልጅ ልጁም ያገለግላሉ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን አገልጋይ ያደርጉታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሕዝቦች ሁሉ ያገለግሉታል፤ እንዲሁም የገዛ ሕዝቡ የሚወድቅበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ለልጁና ለልጅ ልጁ ጭምር ተገዢዎች ይሆናሉ፤ ከዚያም በኋላ የእርሱ ሕዝብ ለኀያላን ሕዝቦችና ለታላላቅ ነገሥታት አገልጋዮች ይሆናሉ።’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጅ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፥ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን ያስገዙታል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 27:7
29 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣ ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።


የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ንግር፤


እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብ በሠረገላ መጥቷል፤ እንዲህም ሲል መለሰ፣ ‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ!’ ”


‘ወደ ባቢሎን ይወሰዳሉ፤ እስከምጐበኛቸውም ቀን ድረስ በዚያ ይቀመጣሉ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በዚያ ጊዜም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’ ”


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሰራዊቱ ሁሉ፣ በግዛቱም ሥር ያሉ መንግሥታትና ሕዝቦች ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በአካባቢዋ የሚገኙትን ከተሞች ይወጉ በነበረ ጊዜ፣ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ሊገድለው ለፈለገው ጠላቱ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።’ ”


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን እንደሚወጋ፣ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው መልእክት ይህ ነው፤


የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ዐምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ዐሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤


የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።


ንጉሥ ሆይ፤ አንተ የነገሥታት ንጉሥ ነህ፤ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ሥልጣንን፣ ኀይልንና ክብርን ሰጥቶሃል፤


ንጉሥ ሆይ፤ ያ ዛፍ አንተ ነህ! ታላቅና ብርቱ ሆንህ፤ ታላቅነትህ አድጎ እስከ ሰማይ ደረሰ፤ ግዛትህም እስከ ምድር ዳርቻ ተንሰራፋ።


ባለዕዳ ያደረግሃቸው ድንገት አይነሡብህምን? ነቅተውስ አያስደነግጡህምን? በእጃቸውም ትወድቃለህ።


አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ፣ “ሕዝቦች ሁሉ፣ የዝሙቷን ቍጣ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos