Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ዕርቃኑን ተኛ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዕለታት አንድ ቀን ከወይን ጠጁም ጠጣ፥ ሰከረም፥ በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ተኛ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዕለታት አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ ልብሱንም አውልቆ ራቊቱን በድንኳን ውስጥ ተኛ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከወ​ይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ ዕራ​ቁ​ቱን ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከወይን ጠጁም ጠጣና ስከረ በድንኳኑም ውስጥ ዕርቁቱን ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:21
13 Referencias Cruzadas  

የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።


አረጋውያን ጭምቶች፣ የተከበሩ፣ ራሳቸውን የሚገዙና በእምነት፣ በፍቅርና በትዕግሥት ጤናማነት ያላቸው እንዲሆኑ ምከራቸው።


ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።


ስለዚህ ተደላድዬ ቆሜአለሁ የሚል ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።


በቀን እንደምንመላለስ በአግባብ እንመላለስ። በጭፈራና በስካር አይሁን፤ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።


ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።


የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር፤ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ።


ስለዚህ ሀብታም እንድትሆን፣ በእሳት የነጠረ ወርቅ እንድትገዛ፣ የዕራቍትነትህ ኀፍረት እንዳይታይ፣ ነጭ ልብስ እንድትለብስና ለማየት እንድትችል ዐይንህን በኵል እንድትኳል እመክርሃለሁ።


ኖኅ ገበሬ ነበረና ወይን ተከለ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios