ዘፍጥረት 29:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ያዕቆብም ራሔልን ለማግኘት ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ለርሷ ካለው ፍቅር የተነሣ፣ ሰባት ዓመት እንደ ጥቂት ቀን ሆኖ ታየው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፥ እርሷንም ይወድዳት ስለ ነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነለት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት። Ver Capítulo |