Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 11:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እንዲህ እንደ አንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ በመናገር ይህን ማድረግ ከጀመሩ፣ ከእንግዲህ ያቀዱትን ሁሉ ማከናወን አያዳግታቸውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታም አለ፦ “እነሆ፥ እነዚህ ሕዝቦች አንድ ወገን ናቸው፥ የሁሉም መነጋገሪያ ቋንቋም አንድ ነው። አሁን ይህን ማድረግ ጀመሩ፥ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንዲህም አለ፤ “እነሆ፥ እነዚህ ሰዎች አንድ ወገን ናቸው፤ መነጋገሪያ ቋንቋቸውም አንድ ነው፤ ይህም ከሚሠሩት የመጀመሪያው ብቻ ነው፤ በዚህ ዐይነት ሊሠሩ ያቀዱትን ሁሉ ማድረግ አያቅታቸውም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እነሆ፥ እነ​ርሱ አንድ ወገን ናቸው፤ ለሁ​ሉም አንድ ቋንቋ አላ​ቸው፤ ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ ጀመሩ፤ አሁ​ንም ያሰ​ቡ​ትን ሁሉ መሥ​ራ​ትን አይ​ተ​ዉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ እነርሱ አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 11:6
12 Referencias Cruzadas  

ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ፣ “ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል” አለ።


በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር።


በክንዱ ብርቱ ሥራ ሠርቷል፤ በልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኗቸዋል፤


አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።


እግዚአብሔር አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ።


እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።


ሦስቱ የኖኅ ልጆች እነዚህ ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚሁ ነው።


የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ወገን ፈጥሮ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ አደረገ፤ የዘመናቸውን ልክና የመኖሪያ ስፍራቸውንም ዳርቻ ወሰነላቸው።


ሂዱና ወደ መረጣችኋቸው አማልክት ጩኹ፤ መከራ በሚያገኛችሁ ጊዜ እስኪ ያድኗችሁ።”


እኩለ ቀንም ላይ ኤልያስ፣ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ፤ አምላክ አይደለም እንዴ! ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ወይም ሥራ በዝቶበት፣ አልያም በጕዞ ላይ ይሆናል፤ ተኝቶም ከሆነ ቀስቅሱት” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር።


“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios