Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 17:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር በሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ ዐብሮህ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ አብሮህ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “እግዚአብሔር አምላክህ ከሚሰጥህ ከተሞች በአንድዋ የሚገኝ ወንድ ወይም ሴት በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አድርጎ ቃል ኪዳኑን ያፈርስ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ሀገ​ሮች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳ​ኑን በማ​ፍ​ረስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከአገርህ ደጆች በማንኛይቱም ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 17:2
26 Referencias Cruzadas  

ይህ የደረሰባቸውም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዘውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመስማት ይልቅ ኪዳኑን ስላፈረሱ ነበር፤ ትእዛዞቹን አላደመጡም፤ ደግሞም አልፈጸሙም።


አባቱ ሕዝቅያስ የደመሰሳቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያ ስፍራዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም ለበኣል መሠዊያዎችን አቆመ፤ የአሼራንም ምስል ዐምዶች ሠራ። እንዲሁም ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።


ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።


“ከእንስሳ ጋራ ሩካቤ ሥጋ የሚፈጽም ሰው ይገደል።


“ለእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ።


ከግብጽ አወጣቸው ዘንድ፣ እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻቸው ጋራ እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ የእነርሱ ባል ሆኜ ሳለሁ፣ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።” ይላል እግዚአብሔር።


ኪዳኔን ያፈረሱትንና በፊቴ የገቡትን የኪዳኑን ቃል ያልፈጸሙትን ሰዎች ሥጋውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ እንዳለፉት፣ እንደ እንቦሳው አደርጋቸዋለሁ።


ለአመንዝራና ለነፍሰ ገዳይ ሴቶች የሚገባውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፤ በመዓቴና በቅናቴ እስከ ደም እበቀልሻለሁ።


እንደ አዳም ቃል ኪዳንን ተላለፉ፤ በዚያም ለእኔ ታማኝ አልነበሩም።


“መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ! ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤


“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ይገደል፤ እርሱንም የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።


ሥርዐቴን ብትንቁ፣ ሕጌን ብታቃልሉ፣ ትእዛዞቼንም ሁሉ ባለመፈጸም ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱ፣


ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ፣ በላያችሁ ሰይፍ በማምጣት እበቀላችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ውስጥ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ቸነፈር እሰድድባችኋለሁ፤ ለጠላትም እጅ ዐልፋችሁ ትሰጣላችሁ።


ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፣ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።


የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከአምላካችን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ጐሣም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አለመገኘቱን አረጋግጡ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ።


መልሱም፣ “የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋራ የገባውን ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው።


ወተትና ማር ወደምታፈስሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፣ ከበለጸጉም በኋላ፣ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።


አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባውን ኪዳን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር የከለከለውን ጣዖት በማንኛውም ዐይነት መልክ ለራሳችሁ አታብጁ።


የሙሴን ሕግ የናቀ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይገደል ነበር።


አምላካችሁ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ኪዳን ብታፈርሱ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብትሰግዱላቸው የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችሁ ይነድዳል፤ ከሰጣችሁም ከመልካሚቱ ምድር በፍጥነት ትጠፋላችሁ።”


እስራኤል በድሏል፤ እንዲጠብቁ ያዘዝኋቸውን ቃል ኪዳኔን ጥሰዋል፤ ዕርም የሆነውን ነገር ወስደዋል፤ ሰርቀዋል፤ ዋሽተዋል፤ የወሰዱትንም ከራሳቸው ንብረት ጋራ ደባልቀዋል።


ዕርሙ የተገኘበት ሰው፣ እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፤ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሷል፤ በእስራኤልም ዘንድ አሳፋሪ ተግባር ፈጽሟልና።’ ”


ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፤ “ይህ ሕዝብ ለቀደሙ አባቶቹ የሰጠሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፈ፣ እኔንም ስላልሰማ፣


በዚህ ጊዜ ኢዮአስ በቍጣ ለገነፈለውና በዙሪያው ለነበረው ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ለበኣል ትሟገቱለታላችሁን? ልታድኑትስ ትሞክራላችሁን? ለርሱ የሚሟገትለት ቢኖር እስከ ጧት ይሙት! እንግዲህ በኣል በርግጥ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ሊከላከል ይችላል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos