Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 7:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እኔም ስመለከት፣ “ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፤ የራሱም ጠጕር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፤ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኰራኵሮቹም ሁሉ እንደሚነድድ እሳት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፥ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፥ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 7:9
34 Referencias Cruzadas  

ራሱና ጠጕሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር።


ልብሱም በምድር ላይ ማንም ዐጣቢ ዐጥቦ ሊያነጣው በማይችልበት ሁናቴ እጅግ ነጭ ሆነ።


በዚያም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሓይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ።


“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”


ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ከዚያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።


“ሌሊት ባየሁት ራእይ፣ የሰውን ልጅ የሚመስል በሰማይ ደመና ጋራ ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።


የምትሰበሰቡትም የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሰዎችን ሁሉ፣ ይኸውም የጌቶችንና የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ እንድትበሉ ነው።”


ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ካለ በኋላ፣ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ ተቀብሎ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።


ነቢይ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር ከዘሮቹ አንዱን በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል የገባለት መሆኑን ዐወቀ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል።


ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።


ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።


እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን። አሜን።


ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤ በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል።


ከርሱ የሰማነው ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በርሱ ዘንድ ከቶ የለም፤ የሚል ነው።


መልኩ እንደ መብረቅ ብሩህ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።


እኔም ወዲያወኑ በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም በሰማይ ዙፋን ቆሟል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበረ።


ቀጥሎም ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ሰዎች ተቀምጠው ነበር፤ ደግሞም ስለ ኢየሱስ ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል የተሰየፉትን ሰዎች ነፍሶች አየሁ። እነርሱ ለአውሬው ወይም ለርሱ ምስል አልሰገዱም፤ በግንባራቸው ወይም በእጃቸው ላይ የአውሬውን ምልክት አልተቀበሉም፤ እነርሱም ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋራ ሺሕ ዓመት ነገሡ።


ከዚያም ሚክያስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


ከዚያም ሚክያስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ የሰንፔር ዙፋን የሚመስል ነገር ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የሰው መልክ የሚመስል ነበር።


ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።


ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።


ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios