ዳንኤል 5:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ አስማተኞችን፣ ኮከብ ቈጣሪዎችንና መተተኞችን እንዲያስገቡለት አዘዘ፤ ለባቢሎናውያኑ ጠቢባን እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ጽሕፈት አንብቦ ትርጕሙን የሚነግረኝን ሐምራዊ መጐናጸፊያ አለብሰዋለሁ፤ የወርቅ ሐብልም በዐንገቱ ላይ አጠልቅለታለሁ፤ በመንግሥቴም ላይ ሦስተኛ ገዥ ይሆናል።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 አስማተኞችን፥ ጠንቋዮችንና ኮከብ ቈጣሪዎችን እንዲያስገቡለት በከፍተኛ ድምፅ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ተጠርተው በመጡ ጊዜ ንጉሡ “ይህን ጽሕፈት አንብቦ ትርጒሙን ሊነግረኝ የሚችል ሰው፥ ሐምራዊ መጐናጸፊያ ይለብሳል፤ የወርቅ ኒሻንም ይደረግለታል፤ በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕርግ ይይዛል” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ንጉሡም አስማተኞቹንና ከለዳውያኑን ቃላተኞቹንም ያገቡ ዘንድ በታላቅ ድምፅ ጮኽ፥ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን፦ ይህን ጽሕፈት ያነበበ ፍቺውንም ያሳየኝ ሐምራዊ ግምጃ ይለብሳል፥ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዥ ይሆናል ብሎ ተናገረ። Ver Capítulo |