Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 11:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያከብራል፤ አባቶች የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ከነዚህ ይልቅ፥ ምሽጎችን የሚጠብቅ ባዕድ አምላክን ያከብራል፤ በቀድሞ አባቶቹ ላልታወቀ አምላክ ወርቅ፥ ብር፥ ጌጣጌጥ የከበሩ ድንጋዮችንና ሌሎችንም ውድ ስጦታዎች በማቅረብ ያከብራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በእነዚህ ፋንታ ግን የአምባዎቹን አምላክ ያከብራል፥ አባቶቹም ያላወቁትን አምላክ በወርቅና በብር በዕንቍና በከበረ ነገር ያከብረዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:38
8 Referencias Cruzadas  

ጣዖት የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች፣ የሚሠሩባቸውም ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፤ የሚናገሩላቸው ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም ያፍራሉም።


ሴቶች ለሚወድዱትም ሆነ ለአባቶቹ አማልክት ክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።


በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽጎችን ይወጋል፤ ለርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከብራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ላይ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል።


“ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሣል፤ የሰሜንን ንጉሥ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋራ ተዋግቶ ድል ያደርጋል።


በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጽ ይናገራል።


ጭነቱም፦ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቍ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ልብስ፣ ሐር ልብስ፣ ቀይ ልብስ፣ መልካም ሽታ ያለው ዕንጨት ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ፣ ከውድ ዕንጨት፣ ከናስ፣ ከብረትና ከእብነ በረድ የተሠራ ዕቃ ሁሉ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos