Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 5:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ሄዱ። ኢያቡሳውያንም፣ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፣ “ዕውሮችና ዐንካሶች እንኳ ይከለክሉሃልና ወደዚህች አትገባም” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ዘመቱ። እነርሱም፥ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፥ “ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ስለሚከላከሉህ ወደዚህች አትገባም” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ንጉሡና ሰዎቹ ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ዳዊት ወደዚያ የማይገባ መስሎአቸው የምድሪቱ ነዋሪዎች ዳዊትን “አንተ ወደዚህ ልትገባ አትችልም፤ ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ይመልሱሃል” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በሀ​ገሩ ውስጥ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄዱ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን፥ “ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም” አሉት። ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ወደ​ዚህ አት​ገ​ባም ብለው ተቃ​ወ​ሙት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ንጉሡና ሰዎቹም በአገሩ ውስጥ ከተቀመጡት ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፥ እነርሱም፦ ዳዊት ወደዚህ ሊገባ አይችልም ብለው አስበው ነበርና ዳዊትን፦ ዕውሮችንና አንካሶችን ካላወጣህ በቀር ወደዚህ አትገባም አሉት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 5:6
13 Referencias Cruzadas  

የልዑል አምላክ ካህን የነበረው የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤


በአንተ ጕልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።


ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤ መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።


ከሸለቆው በላይ፣ በድንጋያማው ዐምባ ላይ የምትኖሪ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ወጥቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። “ማን በእኛ ላይ ይወጣል? ማንስ ወደ መኖሪያችን ደፍሮ ይገባል?” የምትሉ ሆይ፤


የሚዋጋችሁን የባቢሎናውያንን ሰራዊት ሁሉ አሸንፋችሁ፣ ቍስለኞች ብቻ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ቢቀሩ እንኳ፤ እነዚህ ሰዎች መጥተው ይህችን ከተማ ያቃጥሏታል።”


ይህ መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ እርሱም አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ አግኝቶት ባረከው፤


ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣


ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋራ በኢየሩሳሌም ዐብረው ይኖራሉ።


ጼላ ኤሌፍ፣ የኢያቡሳውያን ከተማ ኢየሩሳሌም፣ ጊብዓ እንዲሁም ቂርያት ነበሩ፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ከተሞች ናቸው። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየጐሣቸው የወረሱት ይህ ነበር።


የብንያም ልጆች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ ሊያስወጧቸው አልቻሉም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋራ በዚያ ዐብረው ይኖራሉ።


የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት መተው፣ በእሳት አቃጠሏት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos