2 ሳሙኤል 16:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና ሹማምቱን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣው ልጄ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፣ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ እግዚአብሔር በል ብሎት ነውና ይራገም፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣ ልጅ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፥ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ ጌታ በል ብሎት ነውና ይራገም፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ቀጥሎም ዳዊት ለአቢሳና ለመኳንንቱ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የራሴ ልጅ ሊገድለኝ ይፈልጋል፤ ታዲያ በዚህ ብንያማዊ ሰው ስለምን ትደነቃላችሁ? እኔን እንዲረግመኝ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ስለዚህ ተዉት፥ የአሰበውን ያድርግ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ዳዊትም አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንስ ይህ የኢያሚን ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ዳዊትም አቢሳንና ባሪያዎቹን ሁሉ፦ እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፥ ይልቁንስ ይህ የብንያም ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ። Ver Capítulo |