Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 12:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የቤተ ሰቡ ሰው፣ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያስነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ዐብሯቸውም አንዳች ነገር አልበላም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያሰነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እምቢ አለ፤ አብሮአቸውም አንዳች ምግብ አልበላም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች ወደ እርሱ ቀርበው ከመሬት ላይ ሊያስነሡት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከመሬት ላለመነሣትና ከእነርሱም ጋር ምንም ነገር ላለመቅመስ ወሰነ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፥ እርሱ ግን እንቢ አለ፥ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 12:17
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።


እርሱም፣ “አልበላም” በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትየዋ ጋራ ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ፤ ከመሬትም ተነሥቶ በዐልጋ ላይ ተቀመጠ።


አብርሃም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ፣ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አረጋዊ አገልጋዩን እንዲህ አለው፤ “እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤


በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፣ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም፤ ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጕዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ።


ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።


ንጉሡም ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ በዚያም ሌሊት ምግብ ሳይበላ፣ የሚያዝናናውም ነገር ሳይቀርብለት ዐደረ፤ እንቅልፍም ከርሱ ራቀ።


ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ “በሐዘን እንደ ተኰራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios