Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 9:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም። ከዚያም፣ “ይህች የተረገመችን ሴት ተመልከቷት፤ ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ናትና በሚገባ ቅበሯት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ወደ ቤተ መንግሥቱም ገብቶ ተመገበ፤ ከዚህም በኋላ “ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ነችና፥ ያችን የተረገመች ሴት ወስዳችሁ ቅበሩ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ወደ ቤተ መንግሥቱም ገብቶ ተመገበ፤ ከዚህም በኋላ “ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ነችና፥ ያችን የተረገመች ሴት ወስዳችሁ ቅበሩ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም፥ ከዝ​ያም በኋላ፥ “ሂዱ፥ ይህ​ችን የተ​ረ​ገ​መች እዩ​አት፤ የን​ጉሥ ልጅ ናትና ቅበ​ሩ​አት” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በገባም ጊዜ በላ ጠጣም፤ ከዚያም በኋላ “ይህችን የተረገመች እዩ፤ የንጉሥ ልጅ ናትና ቅበሩአት፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 9:34
10 Referencias Cruzadas  

የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኀጢአት እንደ ቀላል ነገር ከመቍጠሩም በላይ የሲዶናውያንን ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።


ኤልያስም አክዓብን፣ “የከባድ ዝናብ ድምፅ ይሰማልና ሂድና ብላ፤ ጠጣም” አለው።


በሚስቱ በኤልዛቤል ተገፋፍቶ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ለማድረግ ራሱን የሸጠ እንደ አክዓብ ያለ ሰው ከቶ አልነበረም።


ኢዩም፣ “ወደ ታች ወርውሯት!” አለ፤ እነርሱም ወረወሯት፤ ፈረሶቹ ሲረጋግጧትም ደሟ በግንቡና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ።


ሊቀብሯት ሲወጡ ግን ከራስ ቅሏ፣ ከእግሯና ከእጇ በቀር ሌላ ያገኙት አልነበረም።


መልእክተኞቹ በንጉሡ ትእዛዝ ተቻኵለው ወጡ፤ ዐዋጁም በሱሳ ግንብ ተላለፈ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፤ የሱሳ ከተማ ግን ግራ ተጋብታ ነበር።


የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤ የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል።


ስማችሁንም፣ የተመረጠው ሕዝቤ ርግማን እንዲያደርገው ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር ይገድላችኋል፤ ለአገልጋዮቹ ግን ሌላ ስም ይሰጣቸዋል።


በዝኆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤ በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ ከሠቡትም ጥጃን ለምትበሉ፤


“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos