Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 8:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን ሁሉ አሰልፎ ወደ ጸዒር ተሻገረ። በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሠረገላ አዛዦቹን ሁሉ የከበቧቸውን ኤዶማውያንን መታ፤ ሰራዊቱም ወደ ድንኳኑ ሸሸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን በመላ አሰልፎ ወደ ጻዒር ዘመተ፤ የኤዶም ሠራዊትም ከበባቸው፤ በሌሊትም እርሱና የሠረገላዎቹ አዛዦች ከበባውን ጥሰው ሲያመልጡ፥ ወታደሮቹ ወደየቤታቸው ተበታተኑ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን በመላ አሰልፎ ወደ ጻዒር ዘመተ፤ የኤዶም ሠራዊትም ከበባቸው፤ በሌሊትም እርሱና የሠረገላዎቹ አዛዦች ከበባውን ጥሰው ሲያመልጡ፥ ወታደሮቹ ወደየቤታቸው ተበታተኑ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኢዮ​ራ​ምም ከሰ​ረ​ገ​ሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ሲሆር አለፈ፤ ተነ​ሥ​ቶም እር​ሱ​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችን አለ​ቆች ከብ​በው የነ​በ​ሩ​ትን የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች አጠ​ፋ​ቸው፤ ሕዝቡ ግን ወደ እየ​ቤቱ ሸሸ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢዮራምም ከሠረገሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ጸዒር አለፈ፤ በሌሊትም ተነሥቶ እርሱንና የሠረገሎቹን አለቆች ከብበው የነበሩትን የኤዶምያስን ሰዎች መታ፤ ሕዝቡ ግን ወደ ድንኳኑ ሸሸ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 8:21
4 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎምን ጫካ ወስደው በትልቅ ጕድጓድ ውስጥ ወርውረው ጣሉት፤ በላዩም ትልልቅ ድንጋይ ከመሩበት። በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ የቤታቸው ሸሹ።


ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፣ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጧል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደ የቤታቸው ሸሽተው ነበር።


የጨው ሸለቆ በተባለው ቦታ ዐሥር ሺሕ ኤዶማውያንን ድል ያደረገ፣ ሴላን በጦርነት የያዘና እስከ ዛሬም ድረስ ዮቅትኤል ተብላ የምትጠራበትን ስም ያወጣላት አሜስያስ ነው።


“ኢየሩሳሌም በጦር ሰራዊት ተከብባ በምታዩበት ጊዜ፣ ጥፋቷ መቃረቡን ዕወቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos