Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም መሸትሸት ሲል ተነሥተው ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውንም አልወሰዱም ነፍሳቸውን ብቻ ለማዳን ሲሉ ሰፈሩን እንዲሁ እንዳለ ትተው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህም በዚያን ቀን ምሽት ሶርያውያን ድንኳኖቻቸውን፥ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን በጠቅላላም ሰፈራቸውን ሁሉ እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተው ሄደዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህም በዚያን ቀን ምሽት ሶርያውያን ድንኳኖቻቸውን፥ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን በጠቅላላም ሰፈራቸውን ሁሉ እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተው ሄደዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ​ዚ​ህም ተነ​ሥ​ተው በጨ​ለማ ሸሹ፤ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሰፈ​ሩን እን​ዳለ ትተው ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድኑ ዘንድ ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህም ተነሥተው በጨለማ ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውንና ፈረሶቻቸውን አህዮቻቸውንና ሰፈሩን እንዳለ ትተው ነፍሳቸውን ያድኑ ዘንድ ሸሹ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 7:7
18 Referencias Cruzadas  

ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።


እግዚአብሔር ከቶ ሊዋሽ አይችልም፤ እርሱ በሁለት በማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ወደ እርሱ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንድናገኝ አድርጓል።


በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሠኘው ይመራዋል።


ከዐዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣ ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።


“የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፤ በሰፈር የዋሉ ሴቶችም ምርኮን ተካፈሉ።


በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጕልበቱም ማንንም አያድንም።


ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ ተከትሎም ያሳድደዋል።


እያንዳንዱ ሰው በሰፈሩ ዙሪያ የተመደበበትን ቦታ እንደ ያዘም ምድያማውያኑ እየጮኹ ሸሹ።


ከግብጽ ያስመጧቸውም አንዱን ሠረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፣ አንዱን ፈረስ በአንድ መቶ ዐምሳ ሰቅል ብር ገዝተው ነው። እነዚህንም ደግሞ ለኬጢያውያንና ለሶርያውያን ነገሥታት ሁሉ ይሸጡላቸው ነበር።


በሰፈር በዕርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተንቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።


እያንዳንዱም በፊቱ የገጠመውን ጠላት ገደለ፤ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዷቸው ጀመር። የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ ግን በፈረሱ ላይ ሆኖ ከጥቂት ፈረሰኞቹ ጋራ አመለጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios