Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 4:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አገልጋዩም አንሥቶ እናቱ ዘንድ አደረሰው፤ ልጁም እስከ እኩለ ቀን ድረስ በእናቱ ጭን ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አገልጋዩም ያን ልጅ ተሸክሞ በመውሰድ ለእናቱ ሰጣት፤ እርሷም እንደ ታቀፈችው ቆይቶ እኩለ ቀን ላይ ሞተ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አገልጋዩም ያን ልጅ ተሸክሞ በመውሰድ ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም እንደ ታቀፈችው ቈይቶ እኩለ ቀን ላይ ሞተ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አን​ሥ​ቶም ወደ እናቱ ወሰ​ደው፤ በጕ​ል​በ​ቷም ላይ እስከ ቀትር ድረስ አስ​ተ​ኛ​ችው፤ ሞተም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አንሥቶም ወደ እናቱ ወሰደው፤ በጕልበትዋም ላይ እስከ ቀትር ድረስ ተቀመጠ፤ ሞተም።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 4:20
14 Referencias Cruzadas  

ወደ ከተማዋ መግቢያ በር ሲደርስም፣ እነሆ፤ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው ከከተማዋ ወጡ፤ ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፤ እናቱም መበለት ነበረች፤ ብዙ የከተማውም ሕዝብ ከርሷ ጋራ ነበረ።


ስለዚህም በግልጽ እንዲህ አላቸው፤ “አልዓዛር ሞቷል፤


ኢየሱስም ማርታን፣ እኅቷንና አልዓዛርን ይወድዳቸው ነበር።


እኅትማማቾቹም፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትወድደው ሰው ታምሟል” ብለው መልእክት ላኩበት።


የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”


እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣ እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።”


“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም!


ከጥቂት ጊዜ በኋላም የባለቤቲቱ ልጅ ታመመ፤ ሕመሙ እየጠናበት ሄደ፣ በመጨረሻም ትንፋሹ ቀጥ አለ።


ዮሴፍም ሕልም ዐለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት።


እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት።


እግዚአብሔርም፣ “የምትወድደውን አንዱን ልጅህን፣ ይሥሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ፤ እኔ በማመለክትህ በአንዱ ተራራ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው” አለው።


አባቱንም፣ “ራሴን! ራሴን!” አለው። አባቱም አገልጋዩን፣ “ተሸክመህ ወደ እናቱ አድርሰው” አለው።


ወደ ላይ ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው ዐልጋ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios