Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 22:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እኔን ትተውኝ ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑና በእጆቻቸው ሥራ ሁሉ ለቍጣ ስላነሣሡኝ፣ ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ በእጃቸው በሠሩአቸው ጣዖቶች ሁሉ እኔን አስቆጥተውኛል፤ ቁጣዬም አይበርድም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ በእጃቸው በሠሩአቸው ጣዖቶች ሁሉ እኔን አስቈጥተውኛል፤ ቊጣዬም አይበርድም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በእጃቸው ሥራ ሁሉ ያስቈጡኝ ዘንድ ትተውኛልና፥ ለሌሎችም አማልክት ዐጥነዋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።’

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 22:17
33 Referencias Cruzadas  

የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ተወ፤ በእግዚአብሔርም መንገድ አልሄደም።


በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቃጥልባቸውን የኰረብታ መስገጃዎች ሠራ፤ በዚህም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለቍጣ አነሣሣው።


እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሣሣና ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሣለቁ፤ ቃሉን ናቁ፤ ነቢያቱንም አቃለሉ።


አሁን ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ተናገርሁት ስፍራ ምራው፤ መልአኬም በፊትህ ይሄዳል፤ ሆኖም የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ፣ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”


በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዟቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋራ ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋራ ማን መኖር ይችላል?” አሉ።


የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዷል፤ እጁን አንሥቶ መትቷቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ”


ከዚያም፣ ‘የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ኪዳን ትተው ሌሎችን አማልክት ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው’ ይላሉ።”


እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣና መቅሠፍት ታላቅ ስለ ሆነ፣ ምናልባት ልመናቸውን በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”


“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።


የተቀረጹ ምስሎቻችሁን፣ የማምለኪያ ዐምዶቻችሁንም ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ለእጃችሁ ሥራ አትሰግዱም።


በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።” መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።


“እግዚአብሔር በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቈጥቶ ነበር፤


አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸው አስቈጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በሞኝ ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ።


በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።


“በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።


ይኸውም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ለመከልከል ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኀጢአታቸውን ሁልጊዜ በራሳቸው ላይ እስከ መጨረሻው እያከማቹ ይሄዳሉ። ቍጣውም በእነርሱ ላይ ያለ ልክ መጥቷል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos