Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 19:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህን ክፈትና እይ፤ ሰናክሬም ሕያው እግዚአብሔርን ለመሳደብ የላከውን ቃል ስማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አቤቱ፥ ጆሮ​ህን አዘ​ን​ብ​ልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዐይ​ን​ህን ክፈ​ትና እይ፤ በሕ​ያው አም​ላክ ላይ ይገ​ዳ​ደር ዘንድ የላ​ከ​ውን የሰ​ና​ክ​ሬ​ምን ቃል ስማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 19:16
11 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህን ክፈትና እይ። ሰናክሬም ሕያው አምላክን ለመሳደብ የላከውን ቃል ሁሉ ስማ።


ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ፈጥነህ አድነኝ፤ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ።


“አሁንም አምላኬ ሆይ፤ በዚህ ስፍራ ወደ ቀረበው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ፣ ጆሮዎችህም የሚያደምጡ ይሁኑ።


ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የጦር አዛዡን ቃል እግዚአብሔር አምላክህ ይሰማ ይሆናል፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሰምቶ ይገሥጸው ይሆናል፤ ስለዚህ አንተም በሕይወት ለተረፉት ቅሬታዎች ጸልይ።’ ”


አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው።


ባሪያህ ወደዚህ ቦታ የሚያቀርበውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’ ወደ አልኸው በዚህ ስፍራ ወዳለው ቤተ መቅደስ ዐይኖችህ ሌትና ቀን የተከፈቱ ይሁኑ።


ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቷልና።


ምናልባት ሕያው አምላክን ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የጦር አዛዡን ቃል እግዚአብሔር አምላክህ ይሰማ ይሆናል፤ እግዚአብሔር አምላክህም ሰምቶ ይገሥጸው ይሆናል፤ ስለዚህ አንተም በሕይወት ለተረፉት ቅሬታዎች ጸልይ።’ ”


ጌታ ሆይ፤ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ የተዘባበቱትን መዘባበት፣ ሰባት ዕጥፍ አድርገህ አስታቅፋቸው።


“እግዚአብሔር ሆይ፤ የአሦር ነገሥታት እውነትም እነዚህን አሕዛብንና ምድራቸውን አጥፍተዋል።


አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለዐላማህ ተሟገት፤ ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንደሚያላግጥብህ ዐስብ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios