Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 14:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ ሚስት እንድትሆነው ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኲርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‘ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ’ ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኲርንችት ሞተች፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት፦ ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም አውሬ አልፎ ኵር​ን​ች​ቱን ረገጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ “የሊባኖስ ኵርንችት፥ ‘ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው፤’ ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊባኖስም አውሬ አልፎ ኵርንችቱን ረገጠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 14:9
15 Referencias Cruzadas  

ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሯል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታትና ስለ ዓሦችም ተናግሯል፤


የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ግን ለይሁዳ ንጉሥ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “አንድ የሊባኖስ ኵርንችት፣ ለአንድ የሊባኖስ ዝግባ፣ ‘ሴት ልጅህን ለልጄ ሚስት እንድትሆነው ስጠው’ አለው፤ ከዚያም አንድ የሊባኖስ ዱር አውሬ መጥቶ ኵርንችቱን በእግሩ ረገጠው።


ስለዚህ እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ እነርሱም በምናሴ አፍንጫ መንጠቆ አገቡበት፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም ወደ ባቢሎን ወሰዱት።


ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤ መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤


እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መካከል ተገለጠለት። ሙሴም ቍጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም እንኳ፣ አለመቃጠሉን አየ።


በሞኞች አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።


በእሾኽ መካከል እንዳለ ውብ አበባ፣ ውዴም በቈነጃጅት መካከል እንዲሁ ናት።


በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣ ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤ የቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የጕጕቶችም መኖሪያ ትሆናለች።


እኔም፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወዮ! እነርሱ ስለ እኔ፣ ‘ተምሳሌት ብቻ ይመስላል’ ይሉኛል” አልሁ።


ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል።


እግር፣ “እኔ እጅ ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?


እስራኤላውያን፣ ያሉበት ሁኔታ እጅግ የሚያሠጋ መሆኑንና ሰራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፣ በየዋሻውና በየእሾኽ ቍጥቋጦው፣ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጕድጓዱ ሁሉ ተደበቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos