Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 12:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኢዮአስ በዘመነ መንግሥቱ ያከናወነው ሌላው ተግባርና የፈጸመው ሥራ ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአስ አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥና ኢዮራም አካዝያስም የቀደሱትን ቅዱስ ነገር፥ እርሱም የቀደሰውን፥ በእግዚአብሔርም ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶርያም ንጉሥ ወደ አዛሄል ላከው። እርሱም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 12:19
10 Referencias Cruzadas  

የቀረው፣ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሥራ ሁሉ፣ ጥበቡም በሰሎሞን የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?


የቀረው የኢዮርብዓም ታሪክ፣ ያደረገው ጦርነትና አገዛዙም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፏል።


የቀረው የሮብዓም አገዛዝ፣ ያደረገውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?


አሳም ከእግዚአብሔር ቤትና ከራሱም ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የቀረውን ብርና ወርቅ በሙሉ ወሰደ፤ ከዚያም በሹማምቱ እጅ በደማስቆ ተቀምጦ ይገዛ ለነበረው፣ ለጠብሪሞን ልጅ፣ የአዚን የልጅ ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ለቤን ሃዳድ ላከ።


የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ ግን አባቶቹ የይሁዳ ነገሥታት ኢዮሣፍጥ፣ ኢዮራም፣ አካዝያስ ለእግዚአብሔር ቀድሰው የለዩአቸውን የተቀደሱ ዕቃዎች በሙሉ፣ እርሱ ራሱ የቀደሳቸው ስጦታዎች እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ቤቶች የተገኘውን ወርቅ ሁሉ ሰብስቦ ለሶርያ ንጉሥ ለአዛሄል ላከለት፤ አዛሄልም ከኢየሩሳሌም ተመለሰ።


ሹማምቱም በርሱ ላይ ዐመፁበት፤ ቍልቍል ወደ ሲላ በሚወስደው መንገድ ላይ በቤት ሚሎ ገደሉት።


አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብርና ወርቅ ዘርፎ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት እንዲሆን ላከለት።


ስለዚህ ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው።


በዚህ ጊዜም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መዝጊያዎችና መቃኖች ላይ የለበጠውን ወርቅ ነቃቅሎ ለአሦር ንጉሥ ሰጠው።


በኢዮራም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos