Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 1:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ አካዝያስ ኤልያስ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሞተ። አካዝያስ ወንድ ልጅ ስላልነበረው፣ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ወንድሙ ኢዮራም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ኤል​ያ​ስም እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ኤልያስም እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል አካዝያስ ሞተ። ልጅም አልነበረውምና በይሁዳ ንጉሥ በኢዮሣፍጥ ልጅ በኢዮራም በሁለተኛው ዓመት ወንድሙ ኢዮራም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 1:17
11 Referencias Cruzadas  

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ገዛ።


የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ በሰማርያ ነገሠ፤ እስራኤልንም ሁለት ዓመት ገዛ።


ሌላው አካዝያስ በዘመኑ ያከናወናቸውና የፈጸማቸው ሥራዎች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ የተጻፉ አይደለምን?


እግዚአብሔር እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ።


በኤልያስ በተነገረው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም ነበርና።


ሠረገላውንም አመንዝሮች በታጠቡበት በሰማርያ ኵሬ ዐጠቡት፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ቃል ደሙን ውሾች ላሱት።


ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች።


ተመልሰውም ይህን ሲነግሩት፣ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለባሪያው ለቴስብያዊው ለኤልያስ፣ በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበሉታል፤


ኢዩ ወደ ሰማርያ በደረሰ ጊዜ፣ ከአክዓብ ቤተ ሰብ በዚያ የቀረውን ሁሉ ገደለ። ለነቢዩ ለኤልያስ በተነገረውም የእግዚአብሔር ቃል መሠረት አጠፋቸው።


ልጁ ኢዮሣፍጥ በርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios