1 ሳሙኤል 6:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ሠረገላውም ወደ ቤትሳሚስ ወደ ኢያሱ ዕርሻ መጥቶ በአንድ ትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈልጠው፣ ሁለቱን ላሞች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር አቀረቡ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሽ ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ ቆመ። በዚያ ስፍራ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ነበር። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈለጡት፤ ላሞቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለጌታ አቀረቡ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ሠረገላውም በቤትሼሜሽ ወደሚኖር ኢያሱ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው እርሻ መጥቶ በትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ሲደርስ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን እንጨት ፈለጡ፤ ላሞቹንም ዐርደው ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡአቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፤ የሰረገላውንም ዕንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኢያሱ እርሻ መጣ፥ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፥ የሰረገላውንም እንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ። Ver Capítulo |