1 ሳሙኤል 6:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን ይዘው እምቧ እምቧ እያሉ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሳሚስ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዦችም እስከ ቤትሳሚስ ድንበር ተከተሏቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው “እምቧ” እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆችም እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው እምቧ እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፥ የፍልስጥኤማውያንም አለቆች እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላቸው ይሄዱ ነበር። Ver Capítulo |