Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 20:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እርሱም ‘መልካም ነው’ ካለ፣ አገልጋይህን የሚያሠጋው የለም፤ ከተቈጣ ግን፣ ክፉ ነገር እንዳሰበብኝ ታረጋግጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርሱም ‘መልካም ነው’ ካለ፥ አገልጋይህን የሚያሰጋው የለም፤ ከተቆጣ ግን፥ ክፉ ነገር እንዳሰበብኝ ታረጋግጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሡም ‘እሺ’ ቢል፥ እኔ አገልጋይህ በሰላም እንደምኖር ዐውቃለሁ፤ ንጉሡ ከተቈጣ ግን ጒዳት ሊያደርስብኝ የወሰነ መሆኑን ታውቃለህ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እር​ሱም፦ መል​ካም ነው ቢል ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ሰላም ይሆ​ናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእ​ርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዕወቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እርሱም፦ መልካም ነው ቢል ለእኔ ለባሪያህ ደኅንነት ይሆናል፥ ቢቆጣ ግን ክፋት ከእርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቆረጠች እወቅ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 20:7
6 Referencias Cruzadas  

አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተ ሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለ ሆነ፣ አስቢበትና የምታደርጊውን አድርጊ፤ እርሱ እንደ ሆነ እንዲህ ያለ ምናምንቴ ሰው ስለ ሆነ፣ ደፍሮ የሚነግረው አንድም ሰው የለም።”


ንጉሡ ከተቀመጠበት በቍጣ ተነሣ፤ የወይን ጠጁንም ትቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ሄደ። ሐማ ግን ንጉሡ ሊያጠፋው ቈርጦ መነሣቱን ስላወቀ፣ ንግሥት አስቴር ሕይወቱን እንድታተርፍለት ለመማጠን በዚያው ቀረ።


ምክሩም አቤሴሎምንና ዐብረውት የነበሩትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሠኘ።


ዮናታንም፣ “ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ነገር እንዳሰበብህ ባውቅ ኖሮ እንዴት ሳልነግርህ እቀራለሁ?” አለው።


ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ እኔም ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው በማድረግ ከእናንተ ዐሥራ ሁለት ሰዎች መረጥሁ።


ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፣ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቈርጦ መነሣቱን ዐወቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios