Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 10:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሳኦልም ጊብዓ ወዳለው ቤቱ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ልባቸውን የነካው ኀያላን ሰዎች ዐብረውት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሳኦልም ጊብዓ ወዳለው ቤቱ ሄደ፤ እግዚአብሔርም ልባቸውን የነካው ኀያላን ሰዎች አብረውት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ እግዚአብሔር ልባቸውን ያነሣሣው ኀያላንም ሳኦልን ተከትለው ሄዱ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን የነ​ካው ኀያ​ላ​ንም ከሳ​ኦል ጋር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ጊብዓ ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካ ኃያላንም ከእርሱ ጋር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 10:26
12 Referencias Cruzadas  

መልእክተኞቹም ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን ለሕዝቡ በተናገሩ ጊዜ፣ ሕዝቡ ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤


ከዚያም ሳሙኤል ወደ አርማቴም ሄደ። ሳኦል ግን ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ወጣ።


ጼላ ኤሌፍ፣ የኢያቡሳውያን ከተማ ኢየሩሳሌም፣ ጊብዓ እንዲሁም ቂርያት ነበሩ፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ከተሞች ናቸው። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየጐሣቸው የወረሱት ይህ ነበር።


አሕዛብ ይህን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፤ ለጌታም ቃል ክብርን ሰጡ፤ ለዘላለም ሕይወት የተዘጋጁትም ሁሉ አመኑ።


ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽም ንጉሥ በፈርዖን ፊት ሞገስና ጥበብን አጐናጸፈው፤ ፈርዖንም በግብጽና በቤተ መንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።


ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።


ከርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፣ “ዕሺ እሰጣችኋለሁ” አለ።


ስለዚህ እስራኤላውያንን ለመውጋት ከየከተሞቻቸው በአንድነት ወደ ጊብዓ መጡ።


ከዚያም እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም ቤተ ሰብ አለቆች እንዲሁም ካህናቱና ሌዋውያኑ ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመሥራት ተዘጋጁ።


ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።


መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤ “በጊብዓ ሰፍረን እናድራለን።” ራማ ደነገጠች፤ የሳኦል ከተማ ጌባዕ ሸሸች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios