Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 18:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አክዓብም አብድዩን፣ “ተነሣና በአገሪቱ ውስጥ ወዳሉት ምንጮችና ሸለቆዎች ሂድ፤ ፈረሶቻችንና በቅሎዎቻችን እንዳይሞቱ በሕይወት እንዲቈዩ ምናልባት ሣር እናገኝ ይሆናል።” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አክዓብም አብድዩን “በአገሩ መካከል ወደ ውሃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:5
11 Referencias Cruzadas  

ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያስገደለች በነበረበት ጊዜ፣ አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ ዐምሳ ዐምሳውን በሁለት ዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውሃ ይሰጣቸው ነበር።


ስለዚህ የሚሄዱበትን ምድር ተከፋፈሉ፤ አክዓብ በአንድ በኩል፣ አብድዩም በሌላ በኩል ሄደ።


ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤


መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤ እነርሱ ወደ ውሃ ጕድጓዶች ይወርዳሉ፤ ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ ራሳቸውን ተከናንበው፣ ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።


መንጎች እንደ ምን ጮኹ፣ ከብቶቹ ተደናግጠዋል፤ መሰማሪያ የላቸውምና፤ የበግ መንጎች እንኳ ተቸግረዋል።


የዱር አራዊት እንኳ ወደ አንተ አለኸለኹ፤ ወራጁ ውሃ ደርቋል፤ ያልተነካውንም መሰማሪያ እሳት በልቶታል።


የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።


ሰዎች ውሃ ፍለጋ ከከተማ ወደ ከተማ ባዘኑ፣ ይሁን እንጂ ጠጥተው አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።


ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣ የበጎች ጕረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios