Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 16:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በዚያም ሰፈር የነበሩ እስራኤላውያን ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን እንደ ሰሙ፣ የሰራዊቱን አዛዥ ዖምሪን በዚያ ዕለት እዚያው ሰፈር ውስጥ በእስራኤል ላይ ማንገሣቸውን ዐወጁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ዚምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዣቸው የነበረውን ዖምሪን አነገሡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ዚምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዣቸው የነበረውን ዖምሪን አነገሡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በሰ​ፈር ያሉ ሕዝ​ቡም “ዘምሪ ከድቶ ኤላን ገደ​ለው፥ በፋ​ን​ታ​ውም ነገሠ” ሲሉ ሰሙ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰ​ፈሩ ውስጥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ዘን​በ​ሪን አነ​ገሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከተማይቱንም ከብበው የነበሩ ሕዝብ ዘምሪ እንደ ዐመፀ፥ ንጉሡንም እንደ ገደለ ሰሙ፤ እስራኤልም ሁሉ በዚያ ቀን በሰፈሩ ውስጥ የሠራዊቱን አለቃ ዖምሪን አነገሡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 16:16
7 Referencias Cruzadas  

ናዳብና መላው እስራኤል በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከብበው ሳሉ፣ ከይሳኮር ነገድ የተወለደው የአኪያ ልጅ ባኦስ ዐምፆ በመነሣት ናዳብን በገባቶን ገደለው።


የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሆኖ ሰባት ቀን ብቻ ገዛ። በዚህ ጊዜ ሰራዊቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ የሆነችውን ገባቶንን ከብቦ ሰፍሮ ነበር።


ከዚያም ዖምሪና ዐብረውት ያሉት እስራኤላውያን ሁሉ ከገባቶን ወደ ላይ ወጥተው ቴርሳን ከበቡ።


የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከርሱ አስቀድሞ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።


አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች። እርሷም የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።


አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች፤ እርሷም የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።


የዖምሪን ሥርዐት፣ የአክዓብን ቤት ልምድ ሁሉ የሙጥኝ ብለሃል፤ ትውፊታቸውንም ተከትለሃል። ስለዚህ አንተን ለውድመት፣ ሕዝብህን ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ አሕዛብም ይሣለቁብሃል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios