Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 1:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ክርስቶስ የላከኝ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጠምቅ አይደለም፤ የክርስቶስም መስቀል ከንቱ እንዳይሆን፣ በሰዎች የንግግር ጥበብ አልሰብክም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ወንጌልን ላስተምር እንጂ ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝም፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር፥ በቃል ጥበብም አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ክርስቶስ የላከኝ የወንጌልን ቃል እንዳስተምር ነው እንጂ እንዳጠምቅ አይደለም፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር የወንጌልን ቃል የማስተምረው ከሰው ጥበብ በተገኘ ንግግር አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ክር​ስ​ቶስ ወን​ጌ​ልን ለመ​ስ​በክ እንጂ ለማ​ጥ​መቅ አል​ላ​ከ​ኝ​ምና፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀ​ሉን ከንቱ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝምና፥ ወንጌልን ልሰብክ እንጂ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ እንዳይሆን በቃል ጥበብ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 1:17
13 Referencias Cruzadas  

ፈሪሳውያን ከዮሐንስ ይልቅ ኢየሱስ ብዙ ደቀ መዛሙርትን እንዳፈራና እንዳጠመቀ ሰሙ፤


ዳሩ ግን ያጠመቀው ኢየሱስ ሳይሆን ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ።


ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ፣ ጴጥሮስ ጥቂት ቀን ከእነርሱ ጋራ እንዲቀመጥ ለመኑት።


ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም።


እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማርነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው።


እንግዲህ ትምክሕታችን ይህ ነው፤ በዚህ ዓለም በተለይም ከእናንተ ጋራ ባለን ግንኙነት፣ ከእግዚአብሔር በሆነ ቅድስናና ቅንነት እንደ ኖርን ኅሊናችን ይመሰክራል፤ ይህም በሰው ጥበብ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ነው።


አንዳንዶች፣ “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ነገር ግን ሰውነቱ ሲታይ ደካማ፣ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይላሉ።


የንግግር ችሎታ ባይኖረኝም እንኳ፣ ዕውቀት ግን አለኝ፤ ይህንም በሁሉ መንገድ በሚገባ ግልጽ አድርገንላችኋል።


ነገር ግን ስውርና አሳፋሪ ነገሮችን ትተናል፤ በማታለል አንመላለስም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ከሐሰት ጋራ አንቀላቅልም፤ ይልቁንም እውነትን በግልጽ እየተናገርን በሰው ሁሉ ኅሊና ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።


ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ መምጣቱ የነገርናችሁ የርሱን ግርማ በዐይናችን አይተን እንጂ፣ በሰዎች ጥበብ የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos