Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 6:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚያን ጊዜ በሩቅ የሚኖሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲታደስ ለመርዳት ይመጣሉ። ቤተ መቅደሱ በታደሰ ጊዜ እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቃላችሁ። ይህም ሁሉ የሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቃል ፍጹም ታዛዦች የሆናችሁ እንደ ሆነ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እነዚያ በሩቅ ያሉት መጥተው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሠራ ያግዛሉ፤ እናንተም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በጥንቃቄ ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በሩቅ ያሉትም መጥተው የጌታን መቅደስ ይሠራሉ፤ የሠራዊት ጌታም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የጌታን ቃል በእውነት ብትታዘዙ ይህ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 6:15
20 Referencias Cruzadas  

ሁሉ ነገር ስለሚሳካላቸውና የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ጻድቃንን የተባረካችሁ ናችሁ በሉአቸው።


ሕዝቦቼ ከሩቅ አገሮች ይመጣሉ፤ ከሰሜንና ከምዕራብ እንዲሁም ከሲኒም።”


በሩቅና በቅርብ ላሉትም ሁሉ ሰላም ይሁን! እኔ ሕዝቤን እፈውሳለሁ፤


እኔ በቊጣዬ ቀጥቼሽ ነበር፤ አሁን ግን እራራልሻለሁ። ባዕዳን ሕዝቦች ቅጽሮችሽን ይሠራሉ፤ ንጉሦቻቸውም ያገለግሉሻል።


ነገር ግን እኔ አምላካቸው ስሆን እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑ ዘንድ ለእኔ መታዘዝ እንደሚገባቸው ብቻ ነገርኳቸው፤ ሁሉ ነገር እንዲከናወንላቸው ከፈለጉም እኔ በሰጠኋቸው ሥርዓት እንዲኖሩ አዘዝኳቸው።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ መኖሪያው ለመምጣት ስለ ተነሣ ሁላችሁም በፊቱ ዝም በሉ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ቅርንጫፉ በቦታው ስለሚስፋፋ ቅርንጫፍ የሚባል ስም ያለው ይህ ሰው ነው። ባለበት ስፍራ በቅሎ ገናና ይሆናል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ እንደገና ይሠራል፤


የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፥ ጌታ አምላካችን ወደ እርሱ ለሚጠራቸው፥ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነው።”


አሁን ግን ይህ እውነት ተገልጦአል፤ በዘለዓለማዊው አምላክ ትእዛዝ ሁሉም አምነው እንዲታዘዙ በነቢያት መጻሕፍት አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁት ተደርጓል።


ይህንንም የሚያደርገው በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን ትእዛዞችና ሕጎች በመጠበቅ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር የተመለስክ እንደ ሆነ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos