Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 2:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ ያልተገረዘው የአሕዛብ ወገን የሕግን ትእዛዝ የሚፈጽም ከሆነ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ይቈጠርለት የለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ያልተገረዙት ሕጉ የሚያዝዘውን የሚፈጽሙ ከሆነ፣ እንደ ተገረዙ አይቈጠሩምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህ ያልተገረዘው የሕግን ሥርዓት ከጠበቀ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ሆኖ አይቆጠርለትምን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አንተ ሳት​ገ​ዘር ብት​ኖር፥ ኦሪ​ት​ንም ብት​ጠ​ብቅ አለ​መ​ገ​ዘ​ርህ መገ​ዘር ትሆ​ን​ል​ሃ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንግዲህ ያልተገረዘ ሰው የሕግን ሥርዓት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ሆኖ አይቈጠርለትምን?

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 2:26
16 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ “አንቺ ሴት እምነትሽ! ትልቅ ነው፤ ስለዚህ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ!” አላት። የሴትዮዋም ልጅ በዚያኑ ሰዓት ዳነች።


መገረዝ በእርግጥ የሚጠቅምህ ሕግን ብትፈጽም ነው፤ ሕግን የምታፈርስ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይቈጠራል።


አንተ የተጻፈ ሕግ እያለህና የተገረዝክም ሆነህ ሕግን ብታፈርስ በሥጋ ያልተገረዘ ሆኖ ሕግን የሚፈጽም የአሕዛብ ወገን ይፈርድብሃል።


እግዚአብሔር አንድ ነው፤ አይሁድንም ሆነ አሕዛብን በእምነት የሚያጸድቅ እርሱ ነው።


ይህንንም ያደረገው በሥጋ ፈቃድ ሳይሆን በመንፈስ ፈቃድ በምንመላለስ በእኛ ትክክለኛው የሕግ ትእዛዝ እንዲፈጸም ነው።


ስለዚህ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም፤ የሚጠቅመውስ አዲስ ፍጥረት መሆን ነው።


ስለዚህ እናንተ ቀድሞ በትውልዳችሁ አሕዛብ የነበራችሁ፥ አይሁድ በሰው እጅ በመገረዛቸው እየተመኩ እናንተን ያልተገረዙ እያሉ ይሰድቡአችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።


በእርሱም በማመናችሁ ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ ኃጢአተኛውን የሥጋ ባሕርይ ለማስወገድ በክርስቶስ የተደረገ ነው እንጂ በሰው እጅ የተደረገ አይደለም።


በመጀመሪያ ከግብጽ ምድር የወጡት ወንዶች ሁሉ ተገርዘው የነበሩ ቢሆኑም እንኳ በበረሓው ጒዞ ጊዜ የተወለዱት ወንዶች አልተገረዙም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos