Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 98:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለንጉሣችን ለእግዚአብሔር አስደሳች የጥሩንባና የቀንደ መለከት ድምፅ አሰሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሡ በጌታ ፊት እልል በሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሙሴና አሮን በክ​ህ​ነ​ታ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ሳሙ​ኤ​ልም ስሙን ከሚ​ጠ​ሩት ጋራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠሩት፥ እር​ሱም መለ​ሰ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 98:6
9 Referencias Cruzadas  

በልብሱና በጭኑ ላይ “የነገሥታት ንጉሥ፥ የጌቶች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።


ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ያሳርጉ ዘንድ አዘዘ፤ መሥዋዕቱንም ማሳረግ ሲጀምሩ ሕዝቡ የምስጋና መዝሙር አቀረበ፤ መዘምራኑም እምቢልታ መንፋትና በዳዊት የዜማ መሣሪያዎች በመታጀብ ማዜም ጀመሩ፤


የገቡትን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ መሆናቸውንም በማረጋገጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በእግዚአብሔር ስም ማሉ፤ ከዚህም በኋላ በጥሩምባና በእምቢልታ ድምፅ ታጅበው በሆታና በእልልታ ደስታቸውን ገለጡ።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios