22 ለእኔ ግን እግዚአብሔር መከታዬ ነው፤ አምላኬ መጠጊያዬ ነው።
22 ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።
22 ጌታ መጠጊያ ሆነኝ፥ አምላኬ የመጠለያዬ ዓለት ነው።
እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።
አምላክ ሆይ! መጠጊያዬ ስለ ሆንክ በአንተ እተማመናለሁ።
የሚያድነኝ ኀያል አምባዬ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እርሱም እምነት የምጥልበት ምሽጌ ስለ ሆነ አልናወጥም።
በከፍተኛ ቦታ ላይ ይኖራሉ። ከለላቸውም እንደ ቋጥኝ ምሽግ ይሆናል ምግባቸውንም በጊዜው ያገኛሉ፤ የሚጠጡትንም ውሃ አያጡም።
ያለ እርሱ የሚጠብቀኝና የሚያድነኝ የለም፤ መከላከያዬም እርሱ ስለ ሆነ ከቶ አልናወጥም።
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት መጠጊያ ነው፤ በመከራ ጊዜም መከላከያ አምባ ነው።
ሕዝቦችን የሚገሥጸው አይቀጣምን የሰውን ዘር የሚያስተምረው ዕውቀት የለውምን?
ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ።