Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 89:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ታማኝነቴና ዘለዓለማዊ ፍቅሬ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል። በሥልጣኔም ብርቱ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ታማኝነቴና ምሕረቴ ከርሱ ጋራ ይሆናል፤ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ፥ የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 89:24
15 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር የሰጠን ተስፋ ሁሉ “አዎን” የሚሆነው በክርስቶስ ነው፤ ስለዚህ ነው ለእግዚአብሔር ክብር በክርስቶስ “አሜን” የምንለው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለሚወደኝ ከጠላቶቹ እጅ አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ።


እኔ ከእንግዲህ ወዲህ በዓለም ላይ አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ናቸው። እኔ ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህ የሰጠኸኝ እንደእኛ አንድ እንዲሆኑ ለእኔ በሰጠኸኝ ስምህ ጠብቃቸው። ይላሉ”


“ከዓለም ውስጥ መርጠህ ለሰጠኸኝ ሰዎች የአንተን ማንነት ገለጥኩላቸው፤ እነርሱ የአንተ ነበሩ፤ አንተ እነርሱን ለእኔ ሰጠኸኝ፤ እነርሱም ቃልህን ጠብቀዋል፤


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤ ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም።


ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፤ ከእርሱም ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ከቶ አይፈርስም።


ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤ በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ።


በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ! የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ!


ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ ብሎአል፤ በማዳንህ ስለ ተደሰትኩ፤ በጠላቶቼ ላይ እሳለቃለሁ።


አምላክ ሆይ! በፊትህ ለዘለዓለም እንዲነግሥ አድርገው፤ በዘለዓለማዊው ፍቅርህና በታማኝነትህ ጠብቀው።


አንተ እኔን የወደድክበት ፍቅር በእነርሱ ላይ እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን እነርሱ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ ደግሞም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።”


ስለ ይሁዳ ነገድም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ የይሁዳን ነገድ ጩኸት ስማ፤ ከሌሎች ነገዶች ጋር እንዲተባበር አድርግ፤ የበረታ ኀይል ስጣቸው፤ ከጠላቶቻቸው ጋር በሚዋጉበት ጊዜ ርዳቸው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios