Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 89:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ረዓብ የተባለውን አውሬ ቀጥቅጠህ ገደልከው፤ በታላቁ ኀይልህ ጠላቶችህን በታተንካቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤ በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የዘ​መ​ኖ​ቻ​ች​ንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበ​ዛም ሰማ​ንያ ዓመት ነው፤ ከእ​ነ​ዚህ ቢበዛ ግን ድካ​ምና መከራ ነው፤ የዋ​ህ​ነት ከእኛ አል​ፋ​ለ​ችና፥ እኛም ተገ​ሥ​ጸ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 89:10
12 Referencias Cruzadas  

የመብረቅ ብልጭታን ልከህ ጠላቶችህን በትናቸው፤ ፍላጻዎችህንም በመወርወር አሳዳቸው።


መከታችን እግዚአብሔር ሆይ! ወገኖቼ የአንተን ተበቃይነት እንዳይረሱ፥ አትግደላቸው፤ ነገር ግን በኀይልህ በትናቸው፤ አዋርዳቸውም።


ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤ በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።


እግዚአብሔር ይነሣ! ጠላቶቹም ይበተኑ! የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ!


በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።


ለእኔ በመታዘዝ የሚያገለግሉኝን ሕዝቦች በምመዘግብበት ጊዜ ግብጽንና ባቢሎንን እጨምራለሁ፤ ከኢየሩሳሌም ተወላጆች ጋር የፍልስጥኤምን፥ የጢሮስንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች እጨምራለሁ።


እነሆ እግዚአብሔር ምድሪቱን አፈራርሶ ባድማ ያደርጋታል፤ የዚያችንም ምድር ገጽታ ለዋውጦ ሕዝቦችዋን ይበትናል፤


ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos