Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 73:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥ እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ በአረማመዴም ልወድቅ ትንሽ ቀረኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አስ​ቀ​ድ​መህ የፈ​ጠ​ር​ሃ​ትን ማኅ​በ​ር​ህን፥ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ት​ንም የር​ስ​ት​ህን በትር፥ በው​ስ​ጥዋ ያደ​ር​ህ​ባ​ትን የጽ​ዮ​ንን ተራራ ዐስብ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 73:2
15 Referencias Cruzadas  

“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።


“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።


እግዚአብሔር ከሞት አዳነኝ፤ እንባዬ እንዲቆም አደረገ፤ እግሮቼንም ከመደናቀፍ ጠበቃቸው።


“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።


ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።


እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።


እኔ ግን በታላቅ ምሕረትህ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ ወደ ቤተ መቅደስህ በአክብሮት እሰግዳለሁ።


“እኔ የማዝነው በሰብአዊ ፍጡር ላይ ነውን? ታዲያ፥ ትዕግሥቴ ቢያልቅ ምን ያስገርማል?


ችግር ባልደረሰበት ሰው ዘንድ የተቸገረን ሰው ችግር ማናናቅ ቀላል ነው። ነገር ግን ሊወድቅ የሚንገዳገደውን ሰው ትገፈትሩታላችሁ።


እንዲህም አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቤ አስቤ ነበር፤


መልካሙንና ቅኑን ነገር አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ።


እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”


እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤ ሰውነቴንም በጾም አጐሳቈልኩ፤ ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ ቀረ።


ስለዚህ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ መካከል ወደ ጥፋት ለመድረስ ተቃረብኩ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios