Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 45:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤ ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ ወደ አንተ ይመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፥ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 45:14
13 Referencias Cruzadas  

እንደ አንዲት ንጽሕት ልጃገረድ በድንግልናዋ ለአንድ ባል እንደምትታጭ እኔም እናንተን ለክርስቶስ ስላአጨኋችሁ ስለ እናንተ መንፈሳዊ ቅናት እቀናለሁ።


አንቺ የእኔ ሙሽራ ሆይ! በአትክልት ቦታ ሆነሽ ጓደኞቼ ድምፅሽን ለመስማት ይፈልጋሉ፤ እስቲ ለእኔ ድምፅሽን አሰሚኝ።


አንቺ ሱላማዊት ሆይ! ነዪ ተመለሺ፤ በደንብ አድርገን እንድንመለከትሽ ነዪ ተመለሺ። ሱላማጢስን በሁለት ሠራዊት መካከል እንደሚደረግ ጭፈራ የምትመለከቱአት ለምንድን ነው?


ሥልሳ ንግሥቶች፥ ሰማኒያ ቊባቶችና ከቊጥር በላይ የሆኑ ቈነጃጅት አሉ፤


አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ! ወዳጅሽ ወዴት ሄደ? እኛም አብረንሽ እንድንፈልገው የሄደበትን አቅጣጫ ንገሪን።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ፍቅር ራሱ ፈቅዶ እስኪነሣ ድረስ ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት፤ በፈጣን አጋዘንና በምድረ በዳ ዋልያ ስም ዐደራ እላችኋለሁ።


“የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን።


“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።


“ምርኮ አግኝተው በመካከላቸው እየተከፋፈሉ አይደለምን? አንድ ወይም ሁለት ቈነጃጅት ለያንዳንዱ ወንድ፥ ለሲሣራ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጠ የልብስ ምርኮ፥ ለእኔም ለአንገቴ በአንገቴ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጒርጒር ልብስ፥”


ለአደባባዩ በር ርዝመታቸው ዘጠኝ ሜትር የሆነ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ ይኑረው፤ የሚደግፉትም አራት እግሮች ያሉአቸው አራት ምሰሶዎች ይኑሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios