Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 33:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ፈረስ ለማዳን ከንቱ ተስፋ ነው፤ ከዚያ ሁሉ ኀይሉ ጋር ሊያድን አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጕልበቱም ማንንም አያድንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፥ በኃይሉም ብዛት አያስመልጥም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጻድ​ቃን ጮኹ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ​ቸው፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ሁሉ አዳ​ና​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 33:17
12 Referencias Cruzadas  

ፈረስን ለጦርነት ማዘጋጀት ይቻላል፤ ድልን የሚያጐናጽፍ ግን እግዚአብሔር ነው።


አንዳንዶች በጦር ሠረገሎቻቸው፥ ሌሎችም በፈረሶቻቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ኀይል እንታመናለን።


የእርሱ ደስታ በብርቱ ፈረሶችና፤ በጦረኞች ኀይል አይደለም።


አሦር አያድነንም፥ በጦር ፈረሶችም አንታመንም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእጃችን የሠራነውን ጣዖት ሁሉ ‘አምላክ’ ብለን አንጠራም፤ አምላክ ሆይ! ወላጆቻቸው የሞቱባቸው በአንተ ምሕረትን ያገኛሉ።”


በዚህ ፈንታ በፈጣን ፈረሶች ላይ ተቀምጣችሁ ከጠላቶቻችሁ እጅ ለማምለጥ ታቅዳላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ‘ፈረሶቻችን እጅግ ፈጣኖች ናቸው’ ትሉ ይሆናል፤ ነገር ግን አሳዳጆቻችሁ ከእናንተ የፈጠኑ ይሆናሉ።


በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤


ባራቅ ከሠራዊቱ ጋር አደጋ በጣለ ጊዜ እግዚአብሔር ሲሣራን ከሠረገሎቹና ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በአደናጋሪ ሁከት ላይ እንዲወድቅ አደረገው፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።


“ጠላቶችህን ለመውጋት ስትዘምት፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን፥ ከአንተ የሚበልጥም ሠራዊት ባየህ ጊዜ ከግብጽ ምድር ያወጣህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ አትፍራቸው፤


እነርሱ ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እኛ ግን እንነሣለን፤ ጸንተንም እንቆማለን።


ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios