Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 146:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ጽዮን ሆይ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይነግሣል። እግዚአብሔር ይመስገን!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው። ሃሌ ሉያ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ ለዘለዓለም ይነግሣል፥ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የፈ​ረ​ስን ኀይል አይ​ወ​ድ​ድም፥ በሰ​ውም ጕል​በት ደስ አይ​ለ​ውም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 146:10
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይኖራል፤ ለሌሎች አማልክት የሚሰግዱ ሕዝቦች ግን ከምድሩ ይጠፋሉ።


ግዛትህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። መንግሥትህም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ የታመነ ነው፤ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው።


ኢየሩሳሌም ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! ጽዮን ሆይ! አምላክሽን አመስግኚ!


እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።


በእናንተ መካከል ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ስለ ሆነ በጽዮን የምትኖሩ ሁሉ ‘እልል’ በሉ!”


ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።


በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው!


ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።


በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤


በመንግሥቴ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር በዐዋጅ አዝዤአለሁ፤ “እርሱ ሕያውና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።


“እስራኤል ሆይ! በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ የባዕድ ወታደሮች አይወሩአትም።


ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos