13 ቀይ ባሕርን ከፈለ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
13 ቀይ ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
ባሕሩን ከፍሎ በመካከሉ አሳለፋቸው፤ ውሃው እንደ ግንብ እንዲቆም አደረገ።
እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።
በታላቁ ኀይልህ ባሕሩን ከፈልክ፤ በባሕር የሚኖሩትን የታላላቅ አውሬዎች ራስ ቀጠቀጥክ፤
እስራኤላውያን ግን ውሃው በግራና በቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ ስለ ቆመላቸው በደረቅ ምድር ተሻገሩ።