Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 136:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አገር መርቶ አወጣ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 136:11
11 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እስራኤላውያንን መርቶ አወጣ፤ ሲወጡም ብርና ወርቅ ይዘው ነበር፤ ከነገዶቻቸውም መካከል ወደ ኋላ የቀረ ማንም አልነበረም።


ሕዝቡን አውጥቶ እንደ በጎች አሰማራቸው፤ በበረሓም እንደ በግ መንጋ መራቸው።


አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ።


እግዚአብሔር ሕዝቡን እየጠበቀ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ዕለት ጊዜው ሌሊት ነበር፤ ያም ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።


በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤


ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ”


የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos