135 የፊትህን ብርሃን ለባሪያህ አብራለት፤ ሕግህንም አስተምረኝ።
135 በባሪያህ ላይ ፊትህን አብራ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
135 በባርያህ ላይ ፊትህን አብራ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
“መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ!
ከዚህ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማስተዋል እንዲችሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤ እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
የሠራዊት አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን! እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤ እንድንድን ምሕረትህን አሳየን!
የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን አስተውል፤ እግዚአብሔር ከሁሉ የበለጠ አስተማሪ ነው።
አድራጎቴን ሁሉ ተናዘዝኩ፤ አንተም ሰማኸኝ፤ እንግዲህ ሕግህን አስተምረኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ የአንተን ሕግ አስተምረኝ።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
ከእንስሶች አብልጦ ያስተማረን ከወፎችም ይልቅ ጥበበኞች ያደረገን እርሱ ነው።
የሠራሁት ኃጢአት የትኛው እንደ ሆነ አስተምረኝ፤ በድዬም ከሆነ፥ ዳግመኛ አልሠራም’ ያለው ሰው አለን?
በዚያን ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፤ ጸሎቱንም እግዚአብሔር ይሰማዋል የእግዚአብሔርን ፊት አይቶ ይደሰታል፤ እግዚአብሔርም ስለጽድቁ ዋጋውን ይከፍለዋል።