Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 115:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እናንተ የምትፈሩት ሁሉ የሚረዳችሁና የሚጠብቃችሁ እርሱ ስለ ሆነ በእግዚአብሔር ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ ረዳታቸውና ጋሻቸው እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታን የምትፈሩ፥ በጌታ ታመኑ፥ ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 115:11
11 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ለራሱና ለቤተሰቡ ጽኑ መታመኛና ዋስትና አለው።


የማንኛውም አገር ሰው ቢሆን እግዚአብሔርን የሚፈራና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ ከሆነ እግዚአብሔር ይቀበለዋል።


“እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ሁሉ እውነት ነው፤ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻ ነው።


ከዚህ በኋላ “እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ታናናሾችም ታላላቆችም አምላካችንን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።


እርሱን ደስ የሚያሰኙት በአክብሮት የሚፈሩትና በዘለዓለማዊ ፍቅሩ የሚታመኑ ሰዎች ናቸው።


ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።


እግዚአብሔር የሚፈሩትንና ዘለዓለማዊ ፍቅሩ ተስፋቸው የሆነውን ይመለከታል።


እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት!


የሚፈሩት ሁሉ “የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” ይበሉ።


የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ “የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” ይበሉ።


የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኑ! እናንተም የእግዚአብሔር ካህናት እግዚአብሔርን አመስግኑ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios