39 በጭቈና፥ በችግርና በሐዘን ተሸንፈው በተዋረዱ ጊዜ ግን፥
39 በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ ቍጥራቸው አንሶ፣ ተዋርደው ነበር፤
39 እነርሱ በጭቈና፥ በስቃይና በኃዘን ተዋርደው እያነሱ ሄዱ፥
በዚያም ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤል ግዛት ስፋቱ እንዲቀነስ ማድረግ ጀመረ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ሁሉ ያዘ።
እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን አሠቃቂ መከራ ተመለከተ፤ በእስራኤል ውስጥ ባሪያዎችም ሆኑ ነጻ ሰዎች፥ ረዳት አልነበራቸውም።
ኢዮአካዝ በነገሠበት ዘመን ሁሉ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤላውያንን በመጨቈን ያስጨንቃቸው ነበር፤
ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኀይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።
ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
አምስት የራብ ዓመቶች ገና ስለሚቀሩ አንተና ቤተሰብህ እንስሶችህም ጭምር ራብ እንዳይደርስባችሁ በጌሴም እመግብሃለሁ።’ ”
መንግሥታትንም ታላላቅ ያደርጋቸዋል፤ ያጠፋቸዋልም፤ ሕዝብን ያበዛል፤ ይበታትናልም።