Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 106:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተናል፤ ተሳስተናል፤ በደለኞችም ሆነናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤ በደልን፤ ክፉም አደረግን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአት ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥ ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 106:6
14 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልጠበቁም፤


እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።


ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩባት በዚያች አገር ሳሉ ‘ኃጢአት ሠርተናል፤ በድለናል፤ ዐምፀናልም’ ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ፥


“ነገር ግን የእናንተ ዘሮች የራሳቸውን ኃጢአት፥ እንዲሁም በእኔ ላይ ያመፁትንና የተቃወሙኝን የቀድሞ አባቶቻቸውን ኃጢአት ይናዘዛሉ፤


እንግዲያውስ አባቶቻችሁ የጀመሩትን እናንተም ፈጽሙ።


እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”


በአንተ ላይ በማመፅ ትእዛዞችህን ሁሉ ተላልፈናል፤ በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት የሰጠኸንንም ሕግና ሥርዓት አልጠበቅንም።


አሁን ደግሞ እናንተ በአባቶቻችሁ ስፍራ ተተክታችኋል፤ የእግዚአብሔርንም ቊጣ በእስራኤል ላይ ለማምጣት የተዘጋጀ አዲስ ኃጢአተኛ ትውልድ ሆናችኋል።


“ነገር ግን አምላካችን ሆይ! እስከ አሁን ስለ ሆነው ነገር ሁሉ ምን ማለት እንችላለን? እነሆ፥ አሁንም እንደገና ትእዛዞችህ አላከበርንም፤


እግዚአብሔር ሆይ! እኛ አንተን በድለናል፤ ስለዚህም የራሳችንንና የቀድሞ አባቶቻችንን ኃጢአት በፊትህ እንናዘዛለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios