Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 106:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ሕዝቡን ታድጎአቸዋል፤ እነርሱ ግን በእርሱ ላይ ማመፅን መረጡ፤ ስለዚህ ኃጢአታቸው ለውድቀታቸው ምክንያት ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን ዐመፃን የሙጥኝ አሉ፤ በኀጢአታቸውም ተዋረዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ብዙ ጊዜ አዳናቸው፥ እነርሱ ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በስሕተታቸውም ተዋረዱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ይህን የሚ​ጠ​ብቅ ጥበ​በኛ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይ እንደ ሆነ ያው​ቃል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 106:43
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።


በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።


በክፉ ሥራቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በዚህ ምክንያት መቅሠፍት በመካከላቸው ተነሣ።


ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ ፍልስጥኤማውያን ቊጥጥር ያደርጉባቸው ስለ ነበር በዚያን ዘመን በእስራኤል ብረት አቅልጠው የሚሠሩ ጠቢባን አልነበሩም፤


ከከብቶቻቸውና ከድንኳኖቻቸው ጋር ሲመጡ ያንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውን ለመቊጠር እስከማይቻል ድረስ እጅግ ብዙዎች ነበሩ፤ መጥተውም ምድሪቱን ያጠፉ ነበር።


እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።


ይህም ሁሉ የደረሰባቸው በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ በማመፃቸውና ምክሩንም በመናቃቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios