Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 28:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንድ ሕዝብ ኃጢአተኛ ሲሆን መሪዎች ይለዋወጡበታል፤ ዐዋቂና አስተዋይ መሪ ሲኖረው ግን ለረዥም ጊዜ ጽኑ ሕዝብ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤ አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አገሪቱ ዓመፀኛ ስትሆን መሪዎችዋ ብዙ ሆኑ፥ በአስተዋይና በአዋቂ ሰው ግን ዘመንዋ ይረዝማል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 28:2
14 Referencias Cruzadas  

ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው፤ በዚህ ዐይነት ባዕሻ በናዳብ እግር ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ።


በቊጣዬ ነገሥታትን ሰጥቻችሁ ነበር፤ ነገር ግን በከፍተኛ ቊጣዬ አጠፋኋቸው።


ስለዚህ ንጉሥ ሆይ! በበኩሌ የምመክርህን ስማ፤ ኃጢአት መሥራትን ትተህ መልካም ሥራ መሥራትን አዘወትር፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑ ሰዎች ራራላቸው፤ ይህን ብታደርግ በሰላም የመኖር ዕድሜህ ይረዝምልህ ይሆናል።”


ሕዝባችሁ ቀድሞ ፈራርሰው የነበሩትን ሁሉ እንደገና መልሶ በጥንቱ መሠረት ላይ ይሠራል፤ ስለዚህም እናንተ ‘ቅጽሮችን መልሶ የሚያንጽና ፈራርሰው የነበሩ ቤቶችን የሚያድስ ሕዝብ’ ተብላችሁ ትጠራላችሁ።”


በዚያች ከተማ የሚኖር ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ከተማይቱን በጥበቡ አዳናት፤ ይሁን እንጂ ያንን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።


አሳ በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮርብዓም ልጅ ናዳብ የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሁለት ዓመት ገዛ፤


በእውነተኞች ሰዎች በረከት ምክንያት ከተማ እያደገች ትሄዳለች፤ የክፉ ሰዎች መጥፎ ንግግር ግን ወደ ውድቀት ያደርሳታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios